የእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከ2 ሚሊየን 9መቶ ሺ ብር በላይ በሆነ ወጪ ባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክሎች ግዢ በመፈጸም ገቢ ማድረጉን ገለጸ።

ጳጉሜ 4/2016 ዓ/ም
***************** የእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከ2 ሚሊየን 9መቶ ሺ ብር በላይ በሆነ ወጪ ባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክሎች ግዢ በመፈጸም ገቢ ማድረጉን ገለጸ።
የጽ/ቤቱ ሐላፊ አቶ ብርሃኑ ታቅነዳ እንደገለጹት በቁጥር 17 የሚሆኑ ባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክሎች በ2 ሚሊየን 9መቶ 60 ሺ ብር ግዢ በመፈጸም በዛሬው እለት ገቢ ተደርጓል።
ከጊዜ ወደ ግዜ እያደገ የመጣው የህዝቡ የልማትና የፈጣን አገልግሎት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ወረዳው ከምን ጊዜውም በተሻለ ሁኔታ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ተሽከርካሪዎቹ በወረዳው በገጠር ሊሰሩ የታቀዱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ለማቀላጠፍ ለመስክ አገልግሎት ታስቦ የተገዙ መሆናቸውንም አብራርቷል።
ወረዳው የተመደበለትን ውስን በጀት እንደ እርሾ በማጣጣም የተሽከርካሪ ግዢ መፈጸሙ ለህዝብ ተጠቃሚነት ያለው ቁርጠኝነት አመላከች እንደሆነም ተናግሯል።
የግዢ አፈጻጸሙን የፋይናንስ አሰራርና ህግን መሠረት ያደረገና የግልጽ ጨረታ ስርአትን የተከተለ መሆኑን ጠቁሟል።
ገቢ የተደረጉ ሞተር ሳይክሎች ጽ/ቤቱ ከወረዳው አስተባባሪ አመራር ጋር በመሆን በቅርቡ ለሴክተር መ/ቤቶች የማከፋፈል ስራ እንደሚሰራም አቶ ብርሃኑ ጠቁሟል

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *