የወረዳውን የንፁህ መጠጥ ውሀ አቅርቦት ሽፋን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ አስተዳዳር ገለጸ።

የወረዳውን የንፁህ መጠጥ ውሀ አቅርቦት ሽፋን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ አስተዳዳር ገለጸ።
የካቲት 12/2017
የወረዳው ነዋሪዎች በበኩላቸዉ መንግስት የንፁህ መጠጥ ዉሃ እጥረትን ለመቅረፍ እያደረገ ያለው ጥረት አበረታች በመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
የእኖር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቱ ተክሌ ህብረተሰቡ ከሚጠይቃቸው የልማት ጥያቄዎች መካከል የንፁህ መጠጥ ውሀ አንዱ መሆኑን ገልጸዉ ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ የዉሃ አቅርቦቱን አሁን ካለበት 30 ከመቶ ሽፋን በላይ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
እቅዱን ተግባራዊ ለማደረግ መንግስት ከሚያደርገዉ ጥረት ባሻገር ህበረተቡን በንቃት በማሳተፍ ዉጤታማ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ዋና አስተዳዳሪዉ አስረድተዋል፡፡
ለአብነትም በወረዳዉ ወንጬ ቀበሌ ለዉሃ መሰረተ ልማት የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ለሟሟላት ህበረተሰቡ ላደረገዉ ንቁ ተሳትፎ አቶ መብራቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
የወረዳው ውሀ ማዕድን ኢነርጂ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ብሩክ ሀይሌ በበኩላቸዉ በወረዳው አዲስ የውሀ ግንባታ ስራዎችንና ነባር የወሀ መስመሮችን የመጠገንና የማስፋፋት ተግባራት በስፋት እየተከናወኑ መሆናቸዉን ተናግረዋል።
በወረዳው በሁሉም ቀበሌዎች ህብረተሰቡን በማሳተፍ ንፁህ የመጠጥ ውሀ ተደራሽ ለማድረግ ጽህፈት ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አቶ ብሩክ አክለዉ ገልጸዋል ።
በመንግስትና በህብረተሰቡ ተሳትፎ ከፍተኛ የገንዘብና የጉልበት ተሳትፎ ተደርጎባቸዉ የተገነቡና አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ የውሀ ተቋማት በባለቤትነት ህብረተሰቡ ሊጠብቃቸው እንደሚገባ አቶ ብሩክ አሳስበዋል ።
በወረዳው ወንጬ ቀበሌ አግኝተን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች የንፁህ መጠጥ ውሀ አቅርቦት ችግራቸውን ለመቅረፍ እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች በመሆኑ ተግባሩ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ ተናግረዋል ።
ከዚህ በፊት በቀበሌው የንፁህ መጠጥ ውሀ ባለ መኖሩ ከፍተኛ የጊዜና የጉልበት ብክነት ብሎም የጤና ችግር ይገጥማቸው እንደነበረ አብራርተው አሁን ላይ መንግስት፤ የቀበሌው ነዋሪዎችና ተወላጆች በመቀናጀት የውሀ መስመር ዝርጋታ በመጀመሩ መደሰታቸውን ገልፀዋል ።
May be an image of 1 person, studying and textNo photo description available.May be an image of 3 people

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *