ጣቱ ትውልድ በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ መሳተፍ የሚያስችለውን ክህሎት መፍጠር እንደሚገባ የእኖር ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት አስታወቀ።

የካቲት 4/2017 ዓ.ም
===============ወጣቱ ትውልድ በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ መሳተፍ የሚያስችለውን ክህሎት መፍጠር እንደሚገባ የእኖር ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት አስታወቀ።
ጽ/ቤቱ በወረዳው በመገናኛ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ በንግድ ስራ ፍቃደኞች ሊሟሉ የሚገባቸው የሙያ ብቃት መስፈርቶች ለመወሰን በወጣው መመሪያ፣በኤሌክተሮኒክስ አያያዝና ጥገና፣በኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ለሁሉም የኤሌክትሮኒክስ ጥገና እና ሽያጭ ነጋዴዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
የወረዳው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዲንሰፋ ጀማል በዚህ ወቅት እንዳሉት ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ የሙያ ብቃት መስፈርቶች ላይ የሚወጡ መመሪያችን መተግበር እንደሚገባ ተናግረዋል።
በመገናኛ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ በንግድ ስራ ፍቃደኞች ሊሟሉ የሚገባቸው የሙያ ብቃት መስፈርቶች ለመወሰን የወጣው መመሪያ እና አዋጅ በሰፊው አብራርተዋል።
በወረዳው ከሞባይል ጥገና ባሻገር አዳዲስ እና ጥራት ያለው የኢንተርኔት፣የፎቶ ኮፒ፣የኢትዮ-ቴሌኮምና የፖስታ አገልግሎቶችን በማዘመን ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚቻል አስታውቀዋል።
የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማጎልበት ለቀጣይ ትውልድ የዕድገት ጎዳና መሰረት መጣል ነው ሲሉም ገልፀዋል።
ወጣቱ ትውልድ በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ መሳተፍ የሚያስችለውን ክህሎት መፍጠር እንደሚገባም ነው ያመላከቱተት።
ሀላፊው አክለውም በኤሌክትሮኒክስ ጥገናና ሽያጭ ዘርፍ የተሰማሩ ነጋዴዎች በመመሪያው መሰረት ጤናማ እና ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል።
በተያያዘም ኢትዮ ኮደርስ የወጣቶች የዲጂታል ቴክኖሎጂ የአስተሳሰብ አድማስ ማስፋትና ማጎልበት የሚያስችል አለም አቀፍ ኢኒሼቲቭ መሆኑን ጠቁመው፤የዲጂታል ክህሎት ስልጠና መርሀ ግብር እየተከናወ መሆኑን አብራርተዋል።
ስለሆነም ዘርፉ ውጤታማ እንዲሆን የወጣቶች ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
ሰልጣኞች በስልጠና ቆይታቸው ያገኙትን ዕውቀት ተጠቅመው ተግባራዊ ለማድረግ አፅንኦት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸውም ሀላፊው አሳስበዋል።
የኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ፕሮግራም እና በኤሌክትሮኒክስ አያያዝና ጥገና ዙርያ የጽ/ቤቱ የኔትወርክ አድሚኒስተርና ሶፍትዌር አስተባባሪ በወ/ሮ ሙሉ ሻፊ በኩል ስልጠና ተሰጥቷል።
ከተሳታፊዎች መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት ስልጠናው እውቀትና ክህሎት በማስታጠቅና በማብቃት ዘመኑን የዋጀ ትውልድ መገንባት ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ ውጤታማ ስራ ለመስራት እንደሚያስችላቸውም ተናግረዋል።
በመድረኩም የወረዳው ሳ/ኢ/ቴ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዲንሰፋ ጀማል፣የወረዳው ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ነጃ አ/ባሲጥ፣የወረዳው የኤሌክትሮኒክስ ጥገናና ሽያጭ ነጋዴዎች እና የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች መሳታፋቸውን የወ/መ/ኮ ዘግቧል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *