በ2017 ዓ.ም ሆሳእና ከተማ እየተካሄደ ባለው በ2ኛው ዙር የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በልዩ ልዩ ዘመናዊ እና ባህላዊ ስፖርቶች ሻምፒዮና እና ፌስቲቫል የጉራጌ ዞን የስፖርት ልኡካን ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝ ከስፍራው የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
በእግር ኳስ የጉራጌ ዞን በምድብ ’’ለ’’ ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች አንዱን ጨዋታ በማሸነፍ 2ኛው ደግሞ በአቻ ውጤት አራት ነጥብ ይዞ በ2ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
የእስካሁኑ የምድብ ’’ለ’’ ጨዋታዎች ውጤት ጉራጌ ዞን ሁለት ጨዋታ ተጫውቶ 4 ነጥብ በመያዝ 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ምስራቅ ጉራጌ ሶስት ጨዋታ ተጫውቶ 6 ነጥብ በመያዝ አንደኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
ሶስት ጨዋታዎች ተጫውተው ሶስት እኩል ነጥብ ያላቸው የቀቤና እና ማረቆ ልዩ ወረዳዎች በሶስኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን በምድቡ ግርጌ የሚገኘው ሀላባ ዞን ሁለት ጨዋታ ተጫውቶ 1 ነጥብ አስመዝግቧል።
በሌሎች እስከ ዛሬ በተደረጉ ውድድሮች የጉራጌ ዞን ውጤት በሚመለከት
በፓራኦሎምፒክስ 9 ወርቅ 6 ብር 4 ነሃስ ድምር 19 ሜዳሊያ የተገኘ ሲሆን በነገው እለት ቀሪ ውድድሮች ይኖራሉ።
በአትሌቲክስ 5 ወርቅ፣ 6 ብር፣ 2 ነሃስ በድምሩ 13 ሜዳሊያ የተገኘ ሲሆን በነገው እለት ቀሪ ውድድሮች ይኖራሉ።
ወርልድ ቴኳንዶ (በወንዶች) 2 ወርቅ፣ 1 ብር እና 2 ነሃስ በድምሩ 5 ሜዳሊያ የተገኘ ሲሆን በነገው እለት ቀሪ ውድድሮች ይኖራሉ።
በጠረጴዛ ቴኒስ ወንዶች 1 ብር እና 2 የነሃስ በድምሩ 3 ሜዳሊያዎች በማግኘት አጠናቋል፡፡
ጉራጌ ዞን በ2017 ዓ.ም በሆሳእና ከተማ እየተካሄደ ባለው በ2ኛው ዙር የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በልዩ ልዩ ዘመናዊ እና ባህላዊ ስፖርቶች ሻምፒዮና እና ፌስቲቫል ውድድሮች እስካሁን 16 የወርቅ፣ 14 የብር እና 10 የነሃስ በድምሩ 40 ሜዳሊያዎች አግኝቷል።
በቀጣይ ቀናት ቀሪ ውድድሮች ያሉ ሲሆን፡
እግር ኳስ ነገ አርብ 7:00 ሰአት ጉራጌ ዞን ምስራቅ ጉራጌን የሚገጥም ሲሆን ቅዳሜ ጉራጌ ዞን ማረቆ ልዩ ወረዳን የሚገጥም ይሆናል።
በቀሪ ውድድሮች ልኡካን ቡድናችን ድል እንዲቀናው እንመኛለን።
በ2017 ዓ.ም ሆሳእና ከተማ እየተካሄደ ባለው በ2ኛው ዙር የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በልዩ ልዩ ዘመናዊ እና ባህላዊ ስፖርቶች ሻምፒዮና እና ፌስቲቫል የጉራጌ ዞን የስፖርት ልኡካን ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝ ከስፍራው የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
በእግር ኳስ የጉራጌ ዞን በምድብ ’’ለ’’ ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች አንዱን ጨዋታ በማሸነፍ 2ኛው ደግሞ በአቻ ውጤት አራት ነጥብ ይዞ በ2ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
የእስካሁኑ የምድብ ’’ለ’’ ጨዋታዎች ውጤት ጉራጌ ዞን ሁለት ጨዋታ ተጫውቶ 4 ነጥብ በመያዝ 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ምስራቅ ጉራጌ ሶስት ጨዋታ ተጫውቶ 6 ነጥብ በመያዝ አንደኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
ሶስት ጨዋታዎች ተጫውተው ሶስት እኩል ነጥብ ያላቸው የቀቤና እና ማረቆ ልዩ ወረዳዎች በሶስኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን በምድቡ ግርጌ የሚገኘው ሀላባ ዞን ሁለት ጨዋታ ተጫውቶ 1 ነጥብ አስመዝግቧል።
በሌሎች እስከ ዛሬ በተደረጉ ውድድሮች የጉራጌ ዞን ውጤት በሚመለከት
በፓራኦሎምፒክስ 9 ወርቅ 6 ብር 4 ነሃስ ድምር 19 ሜዳሊያ የተገኘ ሲሆን በነገው እለት ቀሪ ውድድሮች ይኖራሉ።
በአትሌቲክስ 5 ወርቅ፣ 6 ብር፣ 2 ነሃስ በድምሩ 13 ሜዳሊያ የተገኘ ሲሆን በነገው እለት ቀሪ ውድድሮች ይኖራሉ።
ወርልድ ቴኳንዶ (በወንዶች) 2 ወርቅ፣ 1 ብር እና 2 ነሃስ በድምሩ 5 ሜዳሊያ የተገኘ ሲሆን በነገው እለት ቀሪ ውድድሮች ይኖራሉ።
በጠረጴዛ ቴኒስ ወንዶች 1 ብር እና 2 የነሃስ በድምሩ 3 ሜዳሊያዎች በማግኘት አጠናቋል፡፡
ጉራጌ ዞን በ2017 ዓ.ም በሆሳእና ከተማ እየተካሄደ ባለው በ2ኛው ዙር የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በልዩ ልዩ ዘመናዊ እና ባህላዊ ስፖርቶች ሻምፒዮና እና ፌስቲቫል ውድድሮች እስካሁን 16 የወርቅ፣ 14 የብር እና 10 የነሃስ በድምሩ 41 ሜዳሊያዎች አግኝቷል።
በቀጣይ ቀናት ቀሪ ውድድሮች ያሉ ሲሆን፡
እግር ኳስ ነገ አርብ 7:00 ሰአት ጉራጌ ዞን ምስራቅ ጉራጌን የሚገጥም ሲሆን ቅዳሜ ጉራጌ ዞን ማረቆ ልዩ ወረዳን የሚገጥም ይሆናል።
በቀሪ ውድድሮች ልኡካን ቡድናችን ድል እንዲቀናው እንመኛለን። መረጃው ከዞ/መ/ኮ/መምሪያ ወሰድን!