የካቲት 14/2017 ዓ.ም
==============
የእኖር ወረዳ ዉሃ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ጽ/ቤት የመስኖ ልማት ተጠቃሚዎች ማህበር ማጠናከር እንደሚገባ ገለጸ።
ጽ/ቤቱ በዛሬው እለት ከFSRP ፕሮግራም ጋር በመተባበር በወረዳው ተርሆኘ ቀበሌ ማዕከል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
የስልጠናው ሰነድ በወረዳው ዉሃ ጽ/ቤት የመስኖ ተቋማት አስተዳደር በሆኑት በአቶ አ/ማሊክ ዉጅራ ቀርቦ ሰፋ ያለ ሀሳብና አስተያየት ተሰጥቶበታል።
አቶ አ/ማሊክ ስልጠናው የመስኖ ዉሃ አያያዝ፣አጠቃቀም፣የመስኖ ዉሃ ተጠቃሚዎች ማህበር የገንዘብ ቁጠባና አስተዳደር እንዲሁም የመስኖ ዉሃ ተጠቃሚዎች ማህበር የአጠቃቀም ህግ ማእቀፍ ላይ ያተኮረ መሆኑን አብራርተዋል።
ስልጠናው ማህበራት የመስኖ ልማት ስራ ክህሎትን በማሳደግና ውጤታማ በማድረግ በዘርፉ የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያለመ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
በስልጠናው የተገኙት የወረዳው FSRP ፕሮግራም አስተባሪ አቶ ጌቱ ኮራ በበኩላቸው የመስኖ ዉሃ ተጠቃሚዎች ማህበር ኮሚቴ አባላት የመስኖ ዉሃ አያያዝና አጠቃቀም፣የገንዘብ ቁጠባና አስተዳደር እንዲሁም የመስኖ ዉሃ ህግ ማእቀፍ እና አሰራር በሚገባ መረዳት እንደሚገባቸው አመላክተዋል።
በስልጠናው የተገኙት የወረዳው ዉሃ ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ አባስ ካሚል በበኩላቸው አርሶአደሩ በዙሪያው ያሉ የውሃ አማራጮችን በተገቢው መጠቀም ያለበት መሆኑን ገልጸዋል።
ሀላፊው አክለውም የመስኖ ልማት ማህበር ኮሚቴ አባላት አባላት ዉሃን በፍትሀዊነትና በስምምነት በመጠቀም፣የመስኖ ልማት አሰራር በመከተል
በዘርፉ የበለጠ ተጠቃሚ ለመሆን መስራት ይገባል ብለዋል።
አቶ አባስ በመጨረሻም በመስኖ ውሃ አጠቃቀም ላይ ያሉ ችግሮችን በማስተካከል ምርትና ምርታማነት ለማረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካል በቅንጅት መስራት ያለበት መሆኑን አመላክተዋል።
በስልጠናው የተገኙ ባለድርሻ አካላት በሰጡት አስተያየት ስልጠናው ጠቃሚና በመስኖ ልማት ስራው ላይ የነበሩ የክህሎትና የግንዛቤ ጉለቶችን ማረም የሚችል መሆኑ ተናግረዋል።
የመስኖ ዉሃ ተጠቃሚ ማህበራት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር የማህበረሰቡን የኑሮ ጫና ለመቀነስ ገበያ ለማረጋጋት መስራት ይገባል ብለዋል።



