የአካባቢ ብክለትንና የአየር መዛባትን በመከላከል ማህበራዊ ደህንነትን ለመጠበቅ በሚደረገው ጥረት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለጸ።

የካቲት 12/2017 ዓ.ም
****************** የአካባቢ ብክለትንና የአየር መዛባትን በመከላከል ማህበራዊ ደህንነትን ለመጠበቅ በሚደረገው ጥረት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለጸ።
በእኖር ወረዳ አካባቢ ጥበቃና ደን ልማት ጽ/ቤት በ FSRP ድጋፍ በአካባቢያዊና በማህበራዊ ደህንነት አጠባበቅ ላይ ያተኮረ ስልጠና በጉማያ አዳራሽ ተሰጥቷል።
የወረዳው አካባቢ ጥበቃና ደን ልማት ጽ/ቤት ሐላፊ አቶ በቀለ በዙ በስልጠናው ላይ እንደ ገለጹት የአካባቢ ብክለትንና የአየር መዛባትን በመከላከል ማህበራዊ ደህንነትን ለመጠበቅ በሚደረገው ጥረት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ገልጿል።
ሰልጣኞች ለአካባቢ ጥበቃ፣ለብዝሃ ህይወት እና ለደን ልማት ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩና ባገኙት አጋጣሚ ሌሎችን በመምከር አካባቢያቸውን ከብክለት እንዲጠብቁም አሳስቧል።
የወረዳው የስርዓተ ምግብ ማሻሻያና ማጠናከሪያ ፕሮግራም ( FSRP )አስተባባሪ አቶ ጌቱ ኮራ እንደተናገሩት ጤናማና የተረጋጋ ህይወት ለመምራት አካባቢን ከብክለት ማጽዳት ወሳኝ መሆኑን በርካታ አብነቶችን አንስተው አብራርቷል።
ፕሮግራሙ የወረዳው ህብረተሰብ በምግብ ራሱን እንዲችልና ኑሮውን በዘላቂነት ለመለወጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም አቶ ጌቱ አመላክቷል።
በመሆኑም በሚከናወኑ ተግባራት ላይ የሚቀርብ ማንኛውም ቅሬታ በግልጸኝነትና በውይይት የሚፈታበት አሰራር መኖሩንም ጠቁሟል።
በምግብ ራስን ለመቻል ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም ጀምሮ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ያመላከቱት አስተባባሪው ከኬሚካል ነጻ የሆነ የቤተሰብ የጓሮ ግብርና ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም አስረድቷል።
የጽ/ቤቱ ሐላፊ አቶ በቀለ በዙ፣የአካባቢ ጥበቃ ስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አክመል አህመድ እና የብዝሃ ህይወት ስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አ/ሰመድ ረሻድ በተመረጡ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ለተሳታፊዎች በሰነድ የተደገፈ ስልጠና ሰጥተዋል።በስልጠናው ላይ ከተወሰኑ ቀበሌዎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *