ደም መለገስ ውድ የሆነውን የሰው ልጅ ህይወት የሚታደግ ከስጦታዎች ሁሉ በላይ የሆነ ታላቅ ስጦታ መሆኑን ደም ለጋሽ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተናገሩ።

የካቲት 7/2017 ዓ.ም
===============ደም መለገስ ውድ የሆነውን የሰው ልጅ ህይወት የሚታደግ ከስጦታዎች ሁሉ በላይ የሆነ ታላቅ ስጦታ መሆኑን ደም ለጋሽ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተናገሩ።
የእኖር ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ከወረዳው ጤና ጽ/ቤት ጋር በመቀናጀት 50 ዩኒት ደም መሰብሰብ መቻሉን ተጠቁሟል።
የእኖር ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ብርዝነሽ ባደታ እንደገለፁት የደም ልገሳ ከደም ለጋሹ ምንም ሳይጎድል፤ውድ የሆነውን የሰው ልጅ ህይወት መታደግ የሚያስችል ስጦታ መሆኑን ገልፀዋል።
ደም በመለገስ የእናቶችና ህፃናት እንደዚሁም በተለያዩ አደጋዎች ለተጎዱ ወገኖችን ህይወት መታደግ እንደሚገባም ተናግረዋል።
በመሆኑም ህብረተሰቡ በስፋት ደም በመስጠት የደም እጥረቱን ለመቅረፍ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ወ/ሮ ብርዝነሽ ጥሪ አቅርበዋል።
የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ ተሾመ ገረመው በዚህ ወቅት እንዳሉት የደም ልገሳ ተግባር አንዳችን ለሌላችን መከታ እና አለኝታችንን የምናሳይበት ነው ሲሉ ጠቁመዋል።
በበጋው የወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት በርካታ መሰል መልካም ተግባራት በችግኝ ተከላ፣በከተማ ጽዳት፣በደም ልገሳ ሰፊ ስራ እየተሰራ እንደሆነም አመላክተዋል።
ደም መለገስ ከበጎ ፍቃድ አገልግሎት መካከል አንዱ ሲሆን ህይወትን የመስጠትና የማስቀጠል ተግባር መሆኑንም አንስተዋል።
ይህ የደም ልገሳ ፕሮግራም ለ3ኛ ዙር የሚለገስ ሲሆን በበጋ በጎ ፍቃድ አገልግሎት 100 ዩኒት ደም ለመሰብሰብ ታቅዶ በዛሬው ዕለት 50 ዩኒት ደም መሰብሰብ መቻሉንም ጨምረው ገልፀዋል።
ደም ከለገሱት በጎ ፍቃደኞች መካከል አቶ መለሰ ደንድር፣አቶ ዘመቻ በርክት እና ወ/ሪት መቅደስ ፍቃዱ አግኝተን ባነጋገርንበት ወቅት እንደተናገሩት ደም መለገስ ውድ የሆነውን የሰው ልጅ ህይወት የሚታደግ ከስጦታዎች ሁሉ በላይ የሆነ ታላቅ ስጦታ መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም አንድም እናት በደም እጥረት ምክንያት እንዳትሞት ህብረተሰቡ በመደበኛነት ደም ሊለግስ ይገባል ብለዋል።
በተካሄደው የደም ልገሳ መርሃ-ግብር የጉንችሬ አንደኛ ደረጃ ሆስፒታል ሀላፊዎችና ባለሙያዎች፣እንደዚሁም የሴክተር ባለሙያዎችና በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተሳትፈዋል ዘገባው የወ/መ/ኮ/ነው
በሚተካ ደም የማይተካው
የሰው ልጅ ህይወት እነታደግ!!!

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *