ሐምሌ 23/2016 ዓ/ም
============== በእኖር ወረዳ “ኤቢ ዞን ትሬዲንግ”የመና እርሻ ኢንቨስትመንት በአሁኑ ወቅት ለ110 ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል መፍጠሩን ገለጸ።
የኤቢ ዞን ትሬዲንግ የጃቱ መና እርሻ ኢንቨትመንት ስራ አስኪያጅ አቶ ገብሩ ለምጂ በመንገድ ልማት ዘርፍ ከ13 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ 15 ኪ/ሜ የአፈር ስራና 14 ኪ/ሜ የጠጠር መንገድ ስራ መሰራቱን ጠቁሟል።
በእርሻው ዘርፍ በ206 ሔ/ር መሬት ላይ አኩሪ አተር፣በቆሎና ቡና እየለማ መሆኑን የገለጹት አቶ ገብሩ ከዚሁ ጎን ለጎን ንብ የማነብ ተግባር እየተከናወነ መሆኑን አብራርቷል።
በአሁኑ ወቅት የስራ ዕድል ከተፈጠረላቸው 110 ዜጎች መካከል 10 የሚሆኑት ቋሚ ሰራተኞች መሆናቸውንም ገልጿል።
ከዚህም በተጨማሪ 40 ሔ/ር የመኸር እርሻ የታረሰ ሲሆን በዚህም ጤፍ፣ቦለቄና የእርግብ አተር ለማልማት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
ስራ አስኪያጁ የግብርና ባለሙያዎች እያደረጉት ያለው ድጋፍና ክትትል አመስግነው በቀጣይም የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አመላክቷል።
