ሰኔ 16/2016 ዓ/ም
============በዛሬው ዕለት ወልቂጤ ሰብስቴሽን ላይ የተገጠመው አዲሱ ዘመናዊ ብሬከር ያልተቆራረጠ የኤሌትሪክ አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችል መሆኑን የጉንችሬ አገልግሎት ማዕከል ስራ አስኪያጅ አቶ ጌታቸው አለሙ ገለጹ።
በኤሌትሪክ አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ዙሪያ በወልቂጤ ሰብስቴሽን ማዕከል ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት ተደርጓል።
በዚህ ወቅት አቶ ጌታቸው አለሙ እንደተናገሩት በአዲስ የተተካው አሮጌው ብሬከር ለደንበኞች ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት የማያስችል እንደነበር ጠቁሟል።
የአሁኑ አዲሱ GIS ብሬከር እንዲሁም ኬብል ያልተቆራረጠ አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችል ወቅቱን የሚመጥን እጅግ ውድና ዘመናዊ መሆኑንም ገልጿል።
አቶ አለሙ ለኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አ/ሆ/ድስትሪክት፣ለወልቂጤ ሰብስቴሽን ሐላፊ ለአቶ ሙጀረብ ዩኑስ እና ለጠቅላላ ባልደረቦቹ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።
በመድረኩ የተገኙት የእኖር ወረዳ አስተዳደር የመሰረተ ልማት ዘርፍ አማካሪ አቶ አድርሴ ተረዳ የመብራት መቆራረጥ ለመከላከል ባህር ዛፍ በማስነሳት መስመር የማጽዳት ስራ እየተከናወነ መሆኑን አብራርቷል።
ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣው የህብረተሰቡ የመብራት ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት(ተደራሽ ለማድረግ)የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸውም አቶ አድርሴ ገልጸዋል።
የጉንችሬ ከተማ መስተዳድር ከንቲባ ጽ/ቤት ሐላፊ አቶ ግርማ ጠንክር በበኩላቸው ከመብራት መቋረጥ ጋር ተያይዞ የሚያጋጥሙ ችግሮች በፍጥነት ለይቶ ለማስተካከል የሚረዱ ቴክኒካል አሰራሮ
ችን አጠናክሮ ማስቀል ተገቢ መሆኑን አስገንዝቧል።
ችን አጠናክሮ ማስቀል ተገቢ መሆኑን አስገንዝቧል።በቀጣይ የተጀመረውን የውይይት መድረክ በማስቀጠልና የመረጃ ግንኙነት ስርዓት በመፍጠር በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተጠቃሚው ህብረተሰብ እርካታ ማሳደግ እንደሚገባም ገልጿዋል።
አንዳንድ የውይይቱ ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች ያቀረቡ ሲሆን በአገልግሎት ላይ ያጋጠሙ ችግሮች ለመፍታት ተቀናጅቶ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
በዕለቱ የተገጠሙ አዳዲስ ዘመናዊ ብሬከሮችና ኬብሎች ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያግዙ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
የማዕከላዊ ኢ/ያ ክልል ኤሌትሪክ ሐይል ስራ አስኪያጅ አቶ ታደሰ ፣የሆሳና ድስትርቢውሽን ሐላፊ አቶ ፍሬው ገዛኸኝ እና የወልቂጤ ሰብስቴሽን ሐላፊ አቶ ሙጀረብ ዩኑስ ከተሳታፊ ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ሐላፊዎቹ በጋራ እንደገለጹት ሁሉም ማዕከላት ከጉንችሬ አገልግሎት ማዕከል ልምድ በመውሰድ ህብረተሰቡ በቅንነት ማገልገል እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በውይይቱ ላይ ከተወሰኑ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የሚመለከታቸው አካላትና የአገልግሎት ማዕከላት ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል