በእኖር ወረዳ በFSRP ፕሮግራም የተዘጋጀ የአርሶ አደሮች የበጋ መስኖ የመስክ ጉብኝት ተካሄደ።

የካቲት 15/2017 ዓ.ም
===============
በእኖር ወረዳ በFSRP ፕሮግራም የተዘጋጀ የአርሶ አደሮች የበጋ መስኖ የመስክ ጉብኝት ተካሄደ።
የእኖር ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ጉቡኝቱ በበጋ መስኖ ልማት በቀበሌዎቹ የተከናወኑ አበረታች ተግባራት ላይ ልምድ ለመለዋወጥ አጋዥ መሆኑንም ጠቁሟል።
በጉብኝቱ የተገኙት የወረዳው የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሞሸዲን አህመድ እንደገለጹት አርሶአደሩ በእጁ ያለው የመሬትና የዉሃ ሀብት በተገቢው መጠቀም በመስኖ ልማት ላይ በትኩረት መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
የግብርና ስራ በአሁን ወቅት ከምንም በላይ አዋጭ በመሆኑ የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ ባሻገር የገቢ ምንጭ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
ዋና ተጠሪው አክለውም በአሁን ወቅት እንደ ወረዳ በመስኖ ስራ ተምሳሌት ሊሆኑ የሚችሉ ወጣቶች እየተፈጠሩ ቢሆንም የበለጠ ማስፋት ይገባልም ነው ያሉት።
የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብድልመጅድ ጀማል በበኩላቸው ጉብኝቱ በአካባቢያችን ያሉ ምቹ ሁኔታዎችን በመጠቀም ምርታማ መሆን እንደሚቻል ያሚያሳይ ነው ብለዋል።
በመሆኑም በተለይም ወጣቶች በአካባቢያቸው ያሉ ኩሬዎችና በተፈጥሮ የተሰጠን ወንዞችን በተገቢው በመጠቀም የዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆኑም መክረዋል።
አርሶአደሩን የስራ ባህሉን በመቀየር ያለቦታቸው የበቀሉ ባህርዛፎችን በማንሳት ወደ እርሻ መቀየርና ማምረት ይገባል ብለዋል።
በወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ መስፍን ወንድሙ በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት ማየት ብቻ ሳይሆን ልምዱን ወስዶ በመስራት ብዙ ሞዴል ቀበሌዎችን መፍጠር ይገባል ብለዋል።
ጉብኝቱ ምርት ማምጣት ብቻ ሳይሆን አዚው ባለንበት ማምረት አንደሚቻል የሚያስተምር ነው ብለዋል።
በጉብኝቱ የተገኙት የወረዳው የFSRP ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ጌቱ ኮራ እንዳሉት አርሶአደሩ በጉብኝቱ ልምድ በመዉሰድ በወረዳው በሁሉም ቀበሌዎች ተሞክሮ ሊሆኑ የሚችሉ የግብርና ስራዎች መፍጠር እንደሚገባ አመላክተዋል።
አቶ ጌቱ አክለውም ወጣቶች፣ሴቶች እንዲሁም የትኛውንም አርሶአደር በግብርናው ዘርፍ ውጤታማና የሀብት ባለቤት ለመሆን የሚችሉ በመሆኑ ግብርና የሀብት አማራጫቸው አድርገዉ እንዲሰሩም አፅንኦት ሰጥቷል።
በተርሆኘ ቀበሌ በበጋ መስኖ የተደራጁ የአመኛት ማህበር ሰብሳቢ አቶ ወልዴ ተክሉና የአበሩስ ማህበር ሰብሳቢ ወ/ሮ መሰረት ረሻድ በሰጡት አስተያየት ዘርፉ በተገቢው ለተጠቀመበት ሰው ከምግብ ዋስትና ባሻገር አዋጪና ትርፋማ መሆኑን ገልጸዋል።
ሌላው በወረዳው መንግስትና በFSRP ፕሮግራም ሙያዊ ድጋፍ፣የግብዓት፣ የኬሚካል አጠቃቀም፣የምርጥ ዘር ድጋፍ፣የመስኖ ክህሎት ስልጠና እየተደረገላቸው መሆኑን አመላክተዋል።
በጉብኙቱ ላይ የፓርቲ አመራሮች፣የወረዳው ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤና ቋሚ ኮሚቴዎች፣ የግብርና ባለሙያዎችና ከየቀበሌው የተውጣጡ አርሶ አርሶአደሮችና ወጣቶች ተገኝቷል።
ዘገባው የወረዳው መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት/ነው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *