ኢትዮጵያን በሁሉም መስክ ተወዳዳሪ ለማድረግ በቁርጠኝነት መስራት ይገባል፡- ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው ጣሰው
**********************
ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት የእኖር መና የግብርና ኢንቨስትመንት በጎበኙበት ወቅት ነው።
ኢትዮጵያን በሁሉም መስክ ተወዳዳሪ ለማድረግ ኢኮኖሚውን በማሳደግ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው ጣሰው ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው ጣሰው እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ ጉራጌ ዞን በባለሐብቶች እየለሙ የሚገኙ የግብርና ልማት ስራዎች ላይ የመስክ ምልከታ አካሂደዋል።
አመራሮቹ በባለሐብቶች እየለሙ የሚገኙ የበቆሎ፣ የሩዝ፣ የሱፍ እና የጤፍ ማሳዎችን ተመልክተዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርናውን በቴክኖሎጂ በመደገፍ እና ያልታረሱ መሬቶችን አሟጦ በመጠቀም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ምርትን ወደ ውጭ ለመላክ እየተሰራ መሆኑን አቶ እንዳሻው ተናግረዋል።
በክልሉ ለግብርና ስራ ምቹ የሆነ የመሬት ሐብት መኖሩን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ይህን በትብብር ለማልማት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።መረጃው የኢቢሲ ነው።




