”ኧሽርሽርየ” “ኧሽረኘ ገያ” ኧወኸመያ (መስቀር) ገያ” ”መስቀል” በጉራጌ ማህበረሰብ በድምቀት ከሚከበሩ በአላት መካከል አንዱ ነው። ይህንን በአል ተከትሎ በብዙ ሁነቶችና ገጠመኞች ታጅቦ የሚመጣ የመጨረሻ ገበያ ፥ ኧሽርሽርየ”፣ “ኧሽረኘ ገያ” በጉንችሬ ከተማ

ዕለተ ሠኞ መስከረም 13 ፣ 2017 ዓ.ም
===================
”ኧሽርሽርየ” “ኧሽረኘ ገያ” ኧወኸመያ (መስቀር) ገያ”
”መስቀል” በጉራጌ ማህበረሰብ በድምቀት ከሚከበሩ በአላት መካከል አንዱ ነው። ይህንን በአል ተከትሎ በብዙ ሁነቶችና ገጠመኞች ታጅቦ የሚመጣ የመጨረሻ ገበያ ፥ ኧሽርሽርየ”፣ “ኧሽረኘ ገያ” በጉንችሬ ከተማ
”ኧሽርሽርየ ገያ” ገበያ ከፈጠሩት ብልሆች መንደር፣ ከጠበብቶች ሃገር በማህበረሰብ የስነልቦና ልህቀት ተገርቶ፣ በባህል ዕሴት እደጥበብ ተሽቆጥቁጦ፣ በበአል ድባብ ታጅቦ፣ ከገበያነት ይልቅ ፌስቲቫል መስሎ የሚውልበት እለት።
የዕለቱ ገበያ ከባድ የሚያደርገው ባለፉት የበአል ገበያዎች ወቅት በተለያየ ምክንያት የሚፈልገውን ሳይሸምት የቆየ ሸማች የሚርመሰመስበት እለት ነው። ለበአል ገበያ ሩቅ ተጉዞ ምርት ያቀረበ ነጋዴ ትሩፉንና ኪሳራውን የሚለይበት ዕለት እንደመሆኑ ሁለቱም የመወሰን ስልጣናቸው በጊዜ ዳኝነት ከመቀማት ለመትረፍ የሚያደርጉት እሽቅድምድም ልዩ ስሜት ይፈጥራል።
መረጋጋት ከጎደለው እንዲሁ የገበያ ሁኔታን መቆጣጠር የሚያስችል የስሜት ብልህነት በሸሸው የግብይት ሂደት የሚውል ገበያ በመሆኑ የእብድ ገበያ “ኧሽረኘ ገያ” የሚል ማህበረሰባዊ መጠሪያ ይዟል። በአይነትና በመጠን ተመሳሳይ የሆኑ ምርቶች በሰአታት ውስጥ የዋጋ መጨመር ይታይባቸዋል ። መልሶ በሰአታት ውስጥ ሲጋሽብ የነበረ ዋጋ ድንገት ማሽቆልቆል ይጀምራል፣ ምንም አይነት የተረጋጋ የዋጋ ተመንና ልክ የለም።
ሸማች የገበያው ሁኔታ በንቃት ይከታተላል። ሻጭም የሸማቹን አመጣጥና የፍላጎት መጠን ካቀረበው ምርት ጋር እያመዛዘነ ይወስናል። ሸማቹ መቀነስን እየጠበቀ ሻጩ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችልበትን ሁኔታ ለመፍጠር ሲጥር ፉክክሩ ይደራል።
”ኧሽርሽርየ ገያ” የተባለው በቀጣይ ቀናት አማራጭ የግብይት ወቅት ስለማያገኝ የዕለቱ ገበያ ያቀረበውን ብቸኛ አማራጭ ለመሸመት የሚጣደፍ ሸማች እና የያዘውን ሽጦ ለመጨረስ በተገደደና ለመሸጥ በሚጓጓ ነጋዴ መካከል የሚደረግ የግብይት ሂደት በመሆኑ ኧሽርሽርት ገያ የሚል ስሜትንም ግብይቱንም የሚገልጥ መጠሪያ ይዟል።
መግዛትና መሸጥ ማህበራዊና ስነልቦናዊ እንዲሁ ኢኮኖሚያዊ ግዴታ በሆንበት የመስቀል (የወኸመያ) ገበያ ፣ የበዓል ትዝታን በሚያጭሩ የግብይት ሁነቶችን ታጅቦ አልፏል።
በዛሬ ዕለት ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር ሲከናወንበት የነበረው የእርድ ከብት ገበያ የዋጋ ሁኔታ ስንመለከት
#በጣም ከፍተኛ ሰንጋ ሽያጭ
80ሺ …120ሺ
ከፍተኛ 60ሺ….75ሺ
መሀከለኛ 50ሺ……60ሺ
ዝቅተኛ ከ40…50ሺ
ከፍተኛ 40ሺ….55ሺ
መካከለኛ ከ35ሺ…..40ሺ
ዝቅተኛ ከ30ሺ….እና በታች
#መሴና ከፍተኛ
ከፍተኛ 35ሺ…55ሺ
መካከለኛ 30ሺ…….40ሺ
ዝቅተኛ ከ25ሺ እና ከዚያ በታች
መረጃው የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚኒኬሽን ነው

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *