የእኖር ወረዳ የመንግስት ኮምዩንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በመረጃ አደረጃጀትና አጠቃቀም ዙሪያ ለቀበሌ መረጃ ማዕከል አስተባባሪዎች እና ለባለድርሻ አካላት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጥቷል።

የካቲት 17/2017 ዓ.ም
================
የእኖር ወረዳ የመንግስት ኮምዩንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በመረጃ አደረጃጀትና አጠቃቀም ዙሪያ ለቀበሌ መረጃ ማዕከል አስተባባሪዎች እና ለባለድርሻ አካላት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጥቷል።
የጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ ጅላሉ ጀማል ፕሮግራሙን ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት ስልጠናው የቀበሌ የመረጃ ማዕከላት በማጠናከር፣የመረጃ ተደራሽነትና ጥራት ለማሳደግ ያለመ ነው ብለዋል።
በመሆኑም በቀበሌ ማዕከል ደረጃ ተግባሩን ለሚመሩ አስተባባሪዎች በመረጃ አደረጃጀትና አጠቃቀም ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንዲሚገባም አመላክቷል።
የስልጠናው ሰነድ በጽ/ቤቱ የመንግስት መረጃ ማዕከልና ድጅታል ሚዲያ አስተዳደር ስራ ሂደት አስተባባሪ በሆኑት በአቶ ትግስቱ ሙራጋ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
አቶ ትግስቱ የመረጃ አያያዝ፣አጠቃቀም በማሻሻል እንዲሁም የህትመትና የዲጂታል ሚዲያዎችን ተደራሽነት በማስፋት ከወቅቱ ጋር መጓዝ ይገባል ብሏል።
በስልጠናው የተገኙ ባለድርሻ አካላት በሰጡት አስተያየት ስልጠናው ወቅቱን የጠበቀና ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም ቀጣይ ለሚሰሩ የመረጃ አያያዝና አጠቃቀም ስራዎች አጋዥና ጠቃሚ መሆኑንም አመላክተዋል።
በስልጠናው የጽ/ቤቱ ሀላፊና ሙያተኞች፣የቀበሌ የመረጃ ማዕከላት አስተባባሪዎች እንዲሁም የተቋሙ የህዝብ ክንፍ ተገኝቷል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *