ህብረተሰቡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን ማጠናከር እንዲችል ቀበሌን ከቀበሌን የሚያገናኝ የመንገድ ልማት ሰራ ላይ በትኩረት እየተከናወነ እንደሚገኝ በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ገለፁ ።

የካቲት 17/2017ዓ.ም
==========ህብረተሰቡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን ማጠናከር እንዲችል ቀበሌን ከቀበሌን የሚያገናኝ የመንገድ ልማት ሰራ ላይ በትኩረት እየተከናወነ እንደሚገኝ በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ገለፁ ።
በወረዳው የመንገድ ተደራሽነትን ችግር ለመቅረፍ መንግስት ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት የጀመረው የመንገድ ልማት ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል ።
የእኖር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቱ ተክሌ የህብረተሰቡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን ማጠናከር እንዲችል ቀበሌን ከቀበሌ የሚያገናኝ መንገድ ልማት ስራ ላይ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል ።
በወረዳው ህብረተሰቡ በገንዘብና በጉልበት የአቅሙን አሻራ እንዲያሳርፍ ተደርጎ በመሰራቱ በመንገድ ልማቱ ስራ ከጊዜ ወደ ጊዜም አበረታች ውጤት እየተመዘገበ መሆኑ ዋና አስተዳዳሪው አብራርተዋል ።
በኢንቨስትመንት ልማቱ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶችም እየተከናወኑ ባሉት የመንገድ ልማት ስራ ውጤታማ ለማድረግ የማሽነሪ ድጋፍ እያደረጉ በመሆኑ በወረዳው መንግስት ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
የእኖር ወረዳ ትራንስፓርት መንገድ ልማት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ተመስገን ኑርጋ በወረዳው የህብረተሰቡ የመንገድ ልማት ችግር ለመቅረፍ በየአመቱ በሚሰሩ ስራዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እውቅና እንድናገኝ አስችሎናል ብለዋል ።
በበጀት አመቱ ያስመዘገበውን መልካም ውጤት ማስቀጠል እንዲቻል በየደረጃው የሚገኘውን ህብረተሰብ በማወያየት ወደ ተግባር ተገብቷል ።
በመሆኑም በስድስት ወር ውስጥ ለማከናወን የታቀደው የጥርጊያ መንገድ በአብዛኛው መፈፀም መቻሉን አቶ ተመስገን አብራርተዋል ።
ከዚህ ቀደም በወረዳው ለመስራት የተጀመሩ መንገዶች ባጠረ ጊዜ ተሰርተው ለአገልግሎት እንዲውሉ እየተደረገ በመሆኑ በዚህ በ2017 ግማሽት አመት ለመስራት የተጀመሩ መንገዶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ ይደረጋል ሲሉ ተናግረዋል ።
ከዚህ ቀደም የተሰሩና ብልሽት የገጠማቸው መንገዶችም ከህዝብና ከመንግስት የተገኘውን በጀት በመጠቀም በተያዘው እቅድ መሰረት ለመጠገን ተችሏል ብለዋል ።
ሁሉም በየአካባቢው የተሰሩ መንገዶች የረጅም ጊዜ አገልግሎት እንዲኖ ራቸው በአግባቡ ሊጠብቃቸው እንደሚገባ ሀላፊው አሳስበዋል።
በወረዳው ወንጬ ቀበሌ እየተሰራ ባለው የጥርጊያ መንገድ ስራ ላይ አግኝተን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት የመንገድ ተደራሽነት ችግር ለመቅረፍ መንግስት ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት እያከናወነው ያለው ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል ።
ለመንገድ ስራው መሳካትም ከመንግስት ጎን በመሆን በከተማም ሆነ በገጠር የሚገኘው ነዋሪ የአቅማቸውን ገንዘብ በማዋጣትና በጉልበት ስራም ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑንም አስተያየት ሰጪዎቹ አክለዋል ።
ከዚህ ቀደም መንገድ ባለመኖሩ በጤናና በሌሎችም ማህበራዊ ችግሮቻቸውን በመቅረፍ ረገድ በርካታእንግልት ይገጥማቸው እንደነበረና አውስተው የመንገዱ መሰራት ችግራቸው ተቀርፎላቸው በቀላሉ ማህበራዊ ትስስራቸውን ሊያጠናክርላቸው እንደሚችል ነዋሪዎቹ አሰረድተዋል ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *