የእኖር ወረዳ ባህልና ቱሪዝም

 

የእኖር ወረዳ ባህል ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ

ወ/ሮ ጨዋነሽ ይማም

የወረዳው  የተፈጥሮ መስህቦችና አራዊቶች   

ባህላዊ ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ቅርሶች የአንድ ማህበረሰብ ማንነት መገለጫና ህዝብን ከህዝብ ማቀራረቢያ ከሆኑ ዋነኛ መሳሪያ ውስጥ ቀዳሚው ከመሆናቸው በተጨማሪ በቱሪስት መስህብነት የገቢ ማስገኛ ምንጭም በመሆን አካባቢን ይጠቅማሉ፡፡በወረዳችን ለቱሪዝም መስህብነት የሚሆኑ ባህላዊና ታሪካዊ ቦታዎች፣ የተፈጥሮ ደኖችና ፍል ዉሃና እንዲሁም ዋሻዎች ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም ዉስጥ የመስህብ ዓይነቶችና ከወረዳው ርዕሰ ከተማ ያላቸዉ ርቀት ከስር ይመልከቱ፡፡

በወረዳው ለቱሪስትነት ሊያገለግሉ የሚችሉ የተፈጥሮ ሀብቶች

ኧቁባይ መስኪድ

ኧቁባይ መስኪድ (ሀይማኖታዊ)የመስህቡ አይነት ሲኖረው እናንጋራ ቀበሌ ውስጥ ይገኛል ከወረዳው ዋና ከተማ ጉንችሬ ያለው ርቀት 15 ኪ.ሜ ነው፡፡

እናንጋራ ቦዥ(ባህላዊ)   

እናንጋራ ቦዥ ባህላዊ  የመስህብ አይነት ሲኖረው እናንጋራ  ቀበሌ ውስጥ ይገኛል ከወረዳው ዋና ከተማ ጉንችሬ ያለው ርቀት 15.5 ኪ.ሜ ነው፡፡

ኧራየ ዋሻ

ኧራየ ዋሻ ኮሰድ ቀበሌ

ገረንቦ ፏፏቴ

ገረንቦ ፏፏቴ ተፈጥሮአዊ የመስህብ አይነት ሲኖረው ገረንቦ ቀበሌ ውስጥ ይገኛል ከወረዳው ዋና ከተማ ጉንችሬ ያለው ርቀት 25.ሜ ነው፡፡

መና ፍል ውሀ

መና ፍል ውሀ ተፈጥሮአዊ ተፈጥሮአዊ የመስህብ አይነት ሲኖረው ጃቱ ቀበሌ ውስጥ ይገኛል ከወረዳው ዋና ከተማ ጉንችሬ ያለው ርቀት 25 ኪ.ሜ ነው፡፡

ወሸ ዝግባ

ወሸ ዝግባ ባህላዊ  የመስህብ አይነት ሲኖረው ወሸ ዘውያር ቀበሌ ውስጥ ይገኛል ከወረዳው ዋና ከተማ ጉንችሬ ያለው ርቀት  7ኪ.ሜ ነው፡፡

ጋሀራድ ጆፈረ

ጋሀራድ ጆፈረ ተፈጥሮአዊ የመስህብ አይነት ሲኖረው ጋሀራድ ቀበሌ ውስጥ ይገኛል ከወረዳው ዋና ከተማ ጉንችሬ ያለው ርቀት 7.ሜ ነው፡፡

አይሴህአርቭ ላማደ ሀውልት

አይሴህአርቭ ላማደ ሀውልት ወንጨ ቀበሌውስጥ ይገኛል፡፡ 

ከረቤድ ዋሻ

ይህ ዋሻ  በእኖር ወረዳ በከረቤድ ቀበሌ ገበሬ ማህበር የሚገኝ ሲሆን ከዞን 40 ኪሜ  ከወረዳ ከተማ 12 ኪሜ ከዋና መንገድ ከጎምሸ 2.5 ኪሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን በምስራቅ ማቃና በምእራብ ጃቱ በሰሜን ጎምሸ በደቡብ ጋርዳሼ ያዋስኑታል፡፡የዋሻው እድሜ በውል ባየታወቅም እድሜ ጠገብ አባቶች ከሆኑት መካከል አቶ በድር ከድር  እንደተናገሩት ዋሻው በጣለያን ወረራ ጊዜ የተቆፈረ እና እነሱም በጊዘው ይመሽጉበት አንደነበር ነግረውናል በዚያን ጊዜ ጣለያናውያን ቦታው   በተለያየ ምክንያት ቦታው ለቀውት ሲሄዱ ቦታው ሌላ አካል እንዳይቆጣጠርው ጥቁር ፍየል አርደው ይገብሩበት ወይም አምልኮ ይሰሩበት እንደነበር በአፈ ታሪክ ይነገራል፡፡ይህ ዋሻ ውሰጥ ለውሰጥ ትንሽ እንደተኬደ በድንጋይ የተሰራ መሰኮት መሰል ነገር ይገኛል እሱን እንደተሸገርን በቁመት ልክ መሄድ የሚያስችል ቦታ ላይ ይደረሳል መተላለፊያ በሮች ይገኛሉ፤ ዋሻዉ ውስጥ ለውስጥ እስከ ጊቤ ሸለቆ ብሄራዊ ፓርክ ድረስ ያሰኬዳል ተብሎ ይገመታል ኢትዮ-ጣለያን ጦርነት ጊዜ ኢትዮጵያ ድል ስትቀናጅ ቦታው ሙሉ በሙሉ ጥለውት ሲወጡ ይህ ታሪካዊ ዋሻ ሙሉ በሙሉ በአካባቢውማህበረሰብ ቁጥጥር ስር ሆኖ ይገኛል፡፡ ዋሻው ልዩ የሚያደርገው ነገር ከአጠገቡ ምንጭ ውሃ በመኖሩእና በአሁን ሰዓት ለማህረሰቡ ትልቅ ፍይዳ እየሰጠ በመገኘቱ ነዉ፡፡

ሲከምሰር ዋሻ

ይህ ዋሻ የሚገኘው በእኖር ወረዳ በጋሳውዴ ቀበሌ ልዩ መንደር ሲከምሰር  በሚባል ቦታ ከወረዳው ከተማ በስተ ምስራቅ እቅጣጫ 1.5 ኪሜ ገባ ብሎ ይገኛል፡፡ ወደ ዋሻው ለመግባት ከመሬት 2.5 ሜትር ከፍ ተብሎ ወደ ውስጥ ሲገባ በግራ በኩል እንደታጠፍን አነስ ያለ ክፍል ይገኛል ፡፡ የተመሰረተበት ዓ.ም በግልፅ ባይታወቅም ነገር ግን እድሜ ጠገብ አባቶች እንደ ተናገሩት ዋሻው ከጣለያን ወረራ በፊት በአማራ ግዛት ጊዜ ህብረተሰቡ ከጠላት ለመታደግ የተለያዩ መሳሪያዎችና ንብረቶቻቸው በመያዝ ይሸሸጉበት እንደነበር ይነገራል ፡፡ በቅርብ ጊዜ ስንመለከት በደርግ ጊዜ የነበሩ  የኢሀፓ አባል መሽገውበት እንደነበር ታሪክ ያስረዳል ፡፡ ይህ ዋሻ ከሌሎች ለየት የሚያደርገው ነገር  በሚያማምሩ ዕፅዋቶች  ትልልቅ አለቶች  ፏፏቴ  እንዲሁም ደብረ ዳሞ የሚያስመስለው መወጣጫ መኖሩ ቀልብ ሳቢነቱ ያጎላዋል፡፡

ሙጃን ፏ ፏ

ሙጃን ፏፏቴ የሚገኘዉ በእኖር ወረዳ ድበር እና በቸሀ ድንበር ላይ ሲሆን እንደዚሁም በእነሞር ወረዳ በሚገኘዉ በኢባራኘ ቀበሌና በእገበኝ ቀበሌ መካከል በዉንቄ ወንዝ ላይ በቸሀ ወረዳ በአሙረ ቀበሌ ድንበር ላይ ይገኛል፡፡ይህ ፏፏቴ ከሌሎች ለየት የሚያደርገዉ በወረዳችን ካሉት ፏፏቴዎች በከፍታዉ የሚወዳደረዉ እንደሌለና በፏፏቴዉ ዙሪያ በጣም ግዙፍ የሆነ ጥብቅ ደን በአረንጓዴ ቀለም ተሸፍኖ በሚያምሩ አእዋፋት ዝማሬ ታጅቦ መንፈስን በሚያድስ ድምጽ የፏፏቴዉን አወራረድ የሚፈጥረወን እንፍሎት በአጠቃላይ በተፈጥሮ የተሰጠዉን ታአምር የሚገርም ለተመልካች ቀልብ የሚስብና የሚማርክ በመሆኑ ወደ ስፍረዉ በመሄድና ተኣምሩን ተመልክተዉ ተደስተዉ ጭንቀታቸዉን ረስተዉ ይመጣሉ፡፡       

ማቃና ጀፎረ

ይህ ጀፎረ የሚገኘው በእነሞርና ኤነር ወረዳ በመቃና ቀበሌ  ሲሆን ከዞን ከተማ ከወልቂጤ 40 ከወረዳ ከተማ 12 -ኪሜ ከዋና መንገድ ጎምሸ 3 ኪሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን በሰሜን ሁረድ በምስራቅ አሞገራ በምእራብ ከረቤድ በደቡብ ወንጨ ያዋስኑታል፡፡መቃና ጀፎረ በጎንዳ ድብር ልዩ መንደር ውስጥ የሚገኝ ሲሆን እጅግ ለዓይን በሚማርክ መልኩ እኩል የተከረከመ አረንጓዴ ሳር በመልበስ ለሁለት ትይዩ መንደሮች መካከል ግርማ ሞገስ ባላቸው ባህላዊ የጉራጌ ጎጆ ቤቶች ታጅቦ የሚገኙ ለጥ ያለ አረንጓዴ ጎዳና አውራ መንገድ ነው፡፡ይህ የመንደር አመሰራረት ጥንት አባቶችን የአንጅነሪነግ አውቀትና ጥበብ በማይታወቅበት ዘመን ከፈጣሪ የተቸሩትን ጥበብ አሻራ የሳረፉበት ነው፡፡      

ገረንቦ ፏፏቴ

ገረንቦ ፏፏቴ የሚገኘው በእኖር ወረዳ ሲሆን ከወርዳ ከተማ ከሆነው ጉንችሬ በስተ ምዕራብ አቅጣጫ ሲሆን በ26 ኪ.ሜ እረቀት ላይ በገረንቦ ቀበሌ ውስጥ ይገኛል ይህ ፏፏቴ ለየት የሚያደርገው በዊንቄ ወንዝ ላይ 6 ገባር ወንዞች ጨምሮ የተለያዩ ገደላ ገደሎች ሸንተረሩን እያሠሰ ውሎ ገረቦ ቀበሌ ሲደርስ የሚገኘው ትልቅ ገደል ቁልቁለት 20 ሲወረወር የሚያሳየው አስደሳችና መንፈስን የሚድስ ህሊናን የሚማርክ ሀሴት የሚፈጥር ቦታ ነው፡፡

የአግያ ቅዱስ ጎርጊስ ቤተክርስትያን

የአግያ ጎርጊስ ቤተክርስትያን በጉራጌ ዞን በእነሞር  ወረዳ በኩነበር ቀበሌ ልዩ መንደሩ አግያ በሚባል ቦታ የሚገኝ ታሪካዊ መስህብ ሲሆን ይህ ጥንታዊ ቤ/ክርስትያን የተመሰረተው 1823 ዓ.ም ነው፡፡ታሪካዊ ቤተክርስትያኑ ከአዲስ አበባ 220 ኪ/ሜ ከዞን ዋና ከተማ ከወልቂጤ 64 ኪ/ሜከወረዳ ከተማ ከጉንችሬ 22 ኪ/ሜ ርቀት ላይ  ተንጣሎ ይገኛል፡፡የቤተክርስትያኑ አስተዳዳሪዎች እንደነገሩን ታሪካዊ ቤተክርስትያኑ አሁን ላይ 193 አመታት አስቆጥሮዋል ይህ ጥንታዊ መስህብ አመት በገባ በወረሃ ሚያዝያ 23 ቀን የሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ አመታዊ ክብረበአሉ በጣም ብዙ መእመናን በተሰባሰቡበት በድምቀት ተከብሮ ይውላል በእለቱም ብዙ ገቢ ይሰበሰባል፡፡ይሁን እንጂ ይሄ ቤተክርስትያን በወረዳችን ካሉ ጥንታዊ ቤተክርስትያኑ በእድሜ ጠገብነቱ  በ3ተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ይህ ታሪካዊ መስህብ በውስጡ በጣም እድሜ ጠገብ ቅርሶች ይገኛሉ፡፡ 

የኮሰድ ዋሻ

 በእኖር ወረዳ ከሚገኙ መስህቦች አንዱ ነው፡፡ዋሻው የሚገኘው በጉንችሬ በ8 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በኮሳድ፣ አንደሆረ ቀበሌ ደንበር ጋንተሪ መንደር ውስጥ ነው፡፡የኮሰድ ዋሻ አራት የተለያዩ በሮች ያሉት ሲሆን አራቱም በሮች ወደ ተላዩ ቦታ የሚያደርሱ መሆኑን ያካባቢው እድሜ ጠገብ ሽማግሌዎች ይነገራሉ፡፡ዋሻው በወቅቱ ከጦርነትና ጠላት ለመሸሸግ ይጠቀሙበት የነበረ ሲሆን በውስጡም የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች እንዲሁም የቤት ውስጥ ቁሳቁሶች የማብሰያና የመመገቢያ እቃዎች እነዳሉ ይነገራሉ፡፡

ጓንታና ዋሻ

ይህ ዋሻ በጓንታና ቀበሌ ከጉስባጃይ ከዋናው መንድ በስተምዕራብ አቅጣጫ 3 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ ከወረዳችን የጉንችሬ ከተማ ለ22 ኪ.ሜ ርቀት ላይ እንዲሁም ከዞኑ ከወልቂጤ 56 ኪ.ሜ ርቀት በጊቤ ብሄራዊ ፓርክ ክልል ውስጥ ይገኛል፡ይህ ዋሻ ብሄራዊ ፓርኩ መግቢያ ላይ እጅግ ግርማ ሞገስ ካለው ኮረብታ ላይ ያረፋ ሲሆን 4ቱ የተለያዩ ውብና ማራኪ መሰኮቶች ዋሻውን ተጠበውና በልዩ ችሎታ ስለመስራቱ ምልክቶች ናቸው፡፡እንዲሁም ዋሻው ዘመናዊ እንጂ እድሜ ጠገብ የማይመስል/ ማራኪ ቦታ አለው፡፡ ዋሻው ከመቶ አምሳ አመት በላይ እድሜ ያለው የሚነገሩት ተላለቅ ሽማግሌዎች የዋሻውን ስፋት ሲገልፁ በድሮ ጊዜ ገብተው የነበሩ ሰዎች መኖራቸውንና ለ12 ሰዓት ያህል ከተጓዙ በኃላ በዋሻው ውስጥ ትልቅ ባህር አጋጥማቸው ወደ ኃላ መመለሳቸውን ይነገራሉ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት በፓርኮ ውስጥ የሚገኙ እንደ አጋዘን አሳማ ኮርኮሌ ጉሬዛ ዝንጅሮ የሜዳ ፍያል ሚደቆና ሌሎችም የዱር እንስሳቶች ቀን  በፓርኩ ውስጥ ውለው ከመሻሹ ወደዚህ ታላቅ ዋሻ እንደሚያደርጉ ያካባቢው መህበረሰብ ይነገራል፡፡

የጓጅ ዋሻ

የጓጅ ዋሻ የሚገኘው በእኖር ወረዳ በኢባራኝቀበሌሲሆንከዞንከተማከወልቂጤ48ከ.ሜከወረዳ ከተማከጉንችሬ19ከ.ሜከውነቄወንዝ2ከ.ሜርቀትለይየሚገኝድንቅዋሻነው፡፡የዚህዋሻአመሰራረትየአፈታሪክመረጃዎችእንደሚያመለክቱት ዋሻው በዋናነት የተቆፈረው የአካባቢው ነዋሪዎች ራሳችው ከጠላት ወረራ ለመከላከል ሲሉ እንደነበር ነው፡፡ይህም ሲባል በአካቢው ዞገ የሚባል ውሃ ነበር ይህ ተፋሳሸ ወንዝ የጠጣ ከብት ቶሎ ያድጋል ተብሎ ይታመን ስለነበር በዚህም ምክንያት የሀድያና የኦሮሞ ከበት አርቢዎች ይህን ውሃ ለማጠጣት ሲሉ ቀድመው አካባቢው በጦርነት ይይዙታል የአገኙትን ይዘርፋሉ ሰዎችንም ይገድላሉ፡፡ስለሆንም በአካባቢው የሚገኙ ጎሳዎች እራሳችው ከወንበዴ ና ከኦሮሞ ጎሳዎች ለመደበቅ ሲሉ የቆፈሩት አንደሆነበአካባቢው የተወለዱ አቶ መደድ ሀሰን ያስረዳሉ፡፡

በረገዛ ዋሻ

ይህ ዋሻ በትልቅነቱና ስፋቱ ይታወቃል ዋሻው ውስጥ ለውስጥ ከካናስ ቀበሌ ተነስቶ አስከ ጋርባዶ እንደሚደርስ ይገልፃሉ፡፡ይህ ዋሻ 6 መቢግያ መውጫ በሮች ያሉት ሲሆን የተሰራው ከፍታ ቦታ ላይ ስለሆነ ወደ በሩ ለመድረስ በወቅቱ ረዥም መሰላል ይጠቀሙ የነበረ መሆኑንና መሰላሉን ጠላት እንዳይጠቀመው ዋሻ ውስጥ እንደገቡ መሰላሉን ይዘወት ይገቡና ሲወጡ ይዘውት ይወጡ እንደነበረም ይነገራል፡፡እንዲሁም በዋሻ ውስጥ ከዋሻዎቹ በተጨማሪ በሀ/ስለሴ ዘመነ መንግስት የተተከሉ እንዲሁም በአሁኑ መንግስት እየተጠበቁ ያሉ ጥብቅ ደኖችም አለ፡፡ ለዚህ ጥብቅ ደን ውስጥ በተለያዩ አይነት የዛፍ አይነቶች አሉ፡፡ከነዚህም ውስጥ ቀርከሀና ብሳና በብዛት የሚገኙ ሲሆን እንዲሁም የሾላና የባህር ዛፍ ይገኛሉ፡፡ በዚህ ጥብቅ ደን ውስጥም አሳማ,ድኩላ,ጦጣ,ዝንጀሮ, ጀርት,ጅብ,እንዲሁም የተለያዩ አይነት ዝሪያዎች ያላቸው አህዋፋት ይገኛሉ፡

በጊቤሸለቆ፣ፓርክ የተለያዩ አራዊቶች፣አዕዋፍት እፅዋት እንደሚገኙበት መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በዚህ ፓርክ ከሚገኙ እንስሳት ውስጥ አጋዘን፣ጉሬዛ፣አንበሳ፣ሚዳቆ፣ጦጣ፣ጉማሬና ዝንጀሮ ሲሆኑ ከአዕዋፍት ደግሞ ቁራ፣ አሞራ፣እርግብ፣ቆቅ፣ጅግራና የመሳሰሉት ይገኛሉ፡፡ግራር፣ጥድ፣ዶቅማ፣ነጭግራር፣ብሳናና ዋንዛ ሳይጠቀሱ የማይታለፉ እፅዋቶች ናቸው፡፡

ማራኪ ስፍራ ”እረኑኬ እና ሻፏሞ ፏፏቴ”
በእኖር ወረዳ የሚገኙ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ መስህቦችን የመጠበቅ፣የማልማትና የመጎብኘት ልምድ መጠናከር እንዳለበት ተገለጸ።
የወረዳው ባህልና ቱሪዝም ልማት ጽ/ቤት ሐላፊና ባለሙያዎች የአሞገራ ቀበሌ ኧረኑኬ ፏፏቴ ፣የሻፏሞ ፏፏቴ፣የተፈጥሮ ጥብቅ ደኖችና ዋሻዎች ጎብኝተዋል።
የወረዳው ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ጨዋነሽ ኢማም በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት በወረዳው በየአካባቢው የሚገኙ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ መስህቦችን የመጠበቅ፣የማልማትና የመጎብኘት ልምድ መጠናከር እንዳለበት ገልጸዋል።
ኧረኑኬ ፏፏቴ፣የብዝኃ መገኛ የሆነው ጥብቅ ደኖችና እና ዋሻ በጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ አሞገራ ቀበሌ ኧረኑኬ መንደር የሚገኝ ሲሆን ከዞኑ 50.5 ኪ.ሜ እንደዚሁም ከወረዳው ዋና ከተማ 8.5 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ታሪካዊ ይዘት ያለው ስፍራ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ፏፏቴው ልዩ ከሚያደርጉት መካከል በተፈጥሮ ድንጋይ የተከበበ መሆኑንና በፏፏቴው ዙሪያ የሚገኙ የተፈጥሮ ደኖች ለፏፏቴዉ ልዩ ድምቀት ሆነዋል ብለዋል።
ወረዳው ከፏፏቴ በተጨማሪ ጥብቅ የተፈጥሮ ደኖች፣ዋሻዎች እና የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች ያሉበት መሆኑን ያነሱት ወ/ሮ ጨዋነሽ የቱባ ባህሎች መገኛ ስፍራ እንደሆነም ጠቁመዋል።
ሌላኛው ሻፏሞ ፏፏቴ በወረዳው ሻፏሞ ቀበሌ ሴባደን መንደር የሚገኝ ሲሆን ከጉንችሬ ከተማ 30 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ነው።
የፏፏቴው የውሃ መጠን እንደየወቅቱ ሁኔታ በበገና በክረምት የሚለያይ ቢሆንም የቱሪስቶችን ቀልብ የሚስብ የተፈጥሮ መስህብ ሀብት እንደሆነም ተናግረዋል።
በፏፏቴው የወረደው ውሃ ታች መሬት ላይ ተንሳፎ ሲታይ እጅግ ማራኪና እጅግ ጥልቅ መሆኑን አስረድተዋል ፡፡
በየትምህርት ቤቱ በተቋቋሙ የሀገርህን ዕወቅ ክበባት አማካኝነት ተማሪዎች በአካባቢያቸው የሚገኙ መስህቦችን እንዲጎበኙ በማድረግ ባህልና ተፈጥሮን አድንቀውና ጠብቀው እንዲያድጉ ማስተማር ያስፈልጋልም ነው ያሉት።
የቱሪስት መስህቦች፣የማህበረሰቡ ባህላዊ ዕሴቶች፣መገልገያ ቁሳቁስ፣የበአላት አከባበር ጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ እየተሰራ ባለው ተግባር ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ሐላፊዋ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ተሳታፊዎች በበኩላቸው በአሞገራ ኧረኑኬ ፏፏቴ፣በሻፏሞ ፏፏቴ፣በተፈጥሮ ጥብቅ ደኖችና ዋሻ በእጅጉ መደሰታቸውን ገልጸው መስህቦችን በማልማት፣በመጎብኘትና በማስተዋወቅ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ማሳደግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ባህላዊ ቁሳቁሶች

ባህላዊ ምግቦች

የጉራጌ ክትፎ
የጉራጌ ጎመን ክትፎ
 “አመኛት/ሽኛት”
 
           “አመኛት/ሽኛት”ክብር/መከባበር ከሚለው የአማርኛ ፍቺ ጋር የበለጠ ተዛማጅ ትርጉም ያለው ከጉራጌ ብሔረሰብ ድንቅና አኩሪ ባህላዊ ዕሴቶች መካከል በዋንኛነት ይገለጻል።
“አመኛት/ሽኛት”እነዚህ ሁለቱ የጉራጊኛ ቃላት በትርጉም ደረጃ ተመሳሳይነት ያላቸው ቢሆንም “አመኛት” በብሔረ ሰቡ ዘንድ በትውልድ ቅብብሎሽ ስር እየሰደደ በዘላቂነት በሚቀጥልበት ወቅት “ሽኛት” ሰፍኗል ተብሎ ይታመናል።ዘላቂ ክብር/መከባበር እየተለመደና እየዳበረ ሲመጣ “ሽኛት”አለ ይባላል።
“አመኛት/ሽኛት በፈጣሪም ሆነ በሰዎች ዘንድ ተወዳጅ የሆነ መልካም ስነምግባር ለመገንባትና በመከባበርና በመተባበር ላይ የተመሰረተ በጎ ተግባር ለመፈጸም የሚያስችል ዕሴት እንደሆነም ይነገራል።
የእኖር ወረዳ የመንግስት ኮ/ጉ/ጽ/ቤት በዚህ ዙሪያ አግኝቶ ካነጋገራቸው ባህል አዋቂ ሽማግሌዎች መካከል አቶ ሙራድ አህመድ፣ አቶ ተመስገን ክብር እና ሌሎችም ይገኙበታል።
ከሰጡን መረጃ የተወሰነውን ጨልፈን እንደሚከተለው ልናስቃኛችሁ ወደናል።
“አመኛት/ሽኛት ከቤተሰብ አንስቶ በየደረጃው የሚገለጹ የተለያዩ ይዘቶች እንዳሉት ይገልጻሉ።ከአለባበስ፣ከአጋጌጥ፣ከአረማመድ፣እንዲሁም ከአመጋገብና ከአነጋገር ጋር በተያያዘ የሚታወቁ መገለጫዎች መኖራቸውንም ይጠቁማሉ።
በቤተሰብ ደረጃ ለአባትና እናት፣ለታላቅ ወንድምና እህት የሚሰጥ ተገቢ የሆነ ክብር አለ።ለአብነት
ምክርን መቀበል፣የተሰጠ ሀላፊነት በአግባቡ መወጣት፣የስራ ድርሻ ተቀብሎ መፈጸም፣
ከስድብ፣ከሁከትና ከጸያፍ ንግግር መቆጠብ የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው።
“አመኛት/ሽኛት’ በሌለበት ቤት “በረካ”(ረድኤት) እንደማይኖርና ጓሮውም ቢሆን በተሰራው ልክ እንደማይለመልምና ቤቱ ለመግባት ሰው ደስተኛ እንደማይሆን፣በአካባቢ ደረጃም ቢሆን በቤተሰቡ አባል ላይ እምነት/ሀላፊነት እንደማይጣል ይታወቃል።
በጉራጌ ብሔረሰብ ዝምድና ለመቀጠል(ትዳር ለመመስረት )ሲታሰብ ከንብረትና ከመልክ ይልቅ
የልጁና የልጅቷ ባህርይ፣በቤተሰባቸው ደረጃ “አመኛት/ሽኛት” ስለመኖሩ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ማጥናት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው።
በአሁኑ ወቅት ባይስተዋልም ከዚህ በፊት ትዳር ሲመሰረት በወላጆች ብርቱ ጥንቃቄ ይፈጸም ስለነበር ሁለቱ ተጋቢዮች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ፊት ለፊት ተገናኝተው የመተዋወቅም ሆነ የመተያነት ፍላጎት አልነበራቸውም።ባህሉም አይፈቅድም ነበር ።ለምን ከተባለ በወቅቱ “አመኛት እንደሌለ ሽኛት እንደተጓደለ ተደርጎ ይወሰድ ስለነበር ነው።
በወጉና በባህሉ መሰረት የሰርጉ እለት ሰርገኞች በቅሎና ፈረስ ይዘው ከየቦታው ተሰባስበው ከሙሽራው ቤት በመገኘት በቅድመ ባህላዊ ጭፈራ ደስታቸውን ሲገልጹ ሙሽራው ግን ሰው እንዳያየው “አመኛት”እንዳይጥስ ጓዳ ውስጥ ይቀመጥ እንደነበር ይነገራል።
ልብሱን እንዲለብስ የነበረው ልምምጥና ልመና አሁን ካለው ሁኔታ ጋር ሲነጻጸር ለመግለጽ ቃላት ያጥራል።በልጅቷም በኩል ቢሆን “አመኛት/ ሽኛት ” እንዳትጥስ ከፍተኛ ጥንቃቄ ስታደርግ እንደነበር ይገለጻል።
ሙሽራው” እንዴት ከወላጆቼ ጋር ተለይቼ እልፍኝ አድራለሁ “በሚል ሽኛት(ቀመጥ) ሙሽሪት ብቻዋን ከአንድ ሳምንት በላይ እልፍኝ ውስጥ ትቀመጥ ነበር።በወላጆቹ ግሳጼና ልመና ከሳምንት በሗላ ገብቶ ማደር ቢጀምርም ሌሊት ጎህ ሳይቀድ በሩን ቀስ አድርጎ ከፍት በመውጣትና ሩቅ ቦታ ሔዶ ተደብቆ በመዋል አመሻሽ ላይ ወደ እልፍኙ ይመለስ ነበር።
ለምን ከተባለ ወላጆቹና የመንደሩ ሰዎች እንዳያዩት ስለሚፈልግ።”ገና ለገና ከታየሁ አይነ ደረቅነቴ
ገሀድ ይወጣል የሚል ጠንካራ እምነት ስላለው ነው።
በብሔረሰቡ ዘንድ መከባበር፣መፈቃቀር፣ መረዳዳትና መቻቻል በሌለበት ዘላቂ ሰላም “ወገሬት”ይሰፍናል ተብሎ ስለማይታሰብ ነው።የጉራጌ ብሔረሰብ ሰላም ወዳድ ነው የሚባለውም በምክንት እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል።
ለጎረ ቤት አስፈላጊውን ክብርና ተገቢውን እገዛ ማድረግ፣የአባቢው ህብረተሰብ ወግና ባህል አክብሮና ጠብቆ በሰላምና በፍቅር ተቻችሎ መኖር “ከአመኛት/ሽኛት የመነጨ ትሩፋት እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል።
ለታላቅ በስተቀኝ በኩል እንዲያልፍ መንገድ መልቀቅ፣ከሗላ ፈጥኖ በመድረስ ያለ አባቶች/እናቶች ፍቃድ ከፊት ቀድሞ አለመሔድ፣ በመምጣት ታላቅን ከፊተ የሆኑትንም ከፊት ማስቀደም፣ሸክምን መጋራት ወይም ማገዝ፣እንቅፋት ካለ ማስወገድ፣ ድንገት የታመሙትን መደገፍ፣የተቸገሩትን መርዳት የመሳሰሉት መንገድ ላይ ከሚሰጡ የክብር አይነቶች ተጠቃሾች ናቸው።
ሴቶች /እናቶች ውሃ ለመቅዳት ወንዝ በሚወርዱበት ወቅት መንገድ ላይ አባቶች ካጋጠማቸው መንገዱን ለቀው ራቅ ብለው ዳር በመያዝ ካልሆነም ቋጥኝ/ ጫካ ውስጥ በመግባት ፊታቸውና ባዶ እንስራቸውን እንዳይታይባቸው መሬት ላይ አንገታቸውን ደፍተው ይቀመጣሉ።ለምን ቢባል በአባቶች/በደረሱ ወንዶች ዘንድ “አመኛት ኤነድ”(ክብር የለሽ/አይነ ደረቅ )የሚል ስያሜ እንዳይሰጣቸው ስለሚጠነቀቁ ነው።
ጉራጌ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከዘመድም ሆነ ከባዳ ጋር ተዋዶ፣ተቻችሎና አልምቶ በሰላምና በፍቅር የመኖር የቆየ ልምድ ያለው የአንድነትና የትጋት ተምሳሌት የሆነ ህዝብ ነው።ለዚህም “አመኛት/ሽኛት”ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቶለታል።
በአሁኑ ወቅት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሸረሸረ የመጣውን ይህ ድንቅ ባህላዊ እሴት መልሶ ለማጠናከርና ለማጎልበት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል እንላለን።ሰላም!!!